Welcome to the Ethiopian Orthodox Tewahido Church Diocese of Washington, Oregon and Idaho

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የልህቀት ማዕከል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን (ኢ.ኦ.ተ.ቤ)፣ የዋሽንግተን፣ ኦሪገን፣ እና ኢዳሆ ሀገረ ስብከት መንፈሳዊ እና ማኅበረሰብ አገልግሎት ማዕከል የልማት ፕሮግራም

አላማው

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የልህቀት ማዕከል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዋሽንግተን፣ ኦሪጎን እና አይዳሆ ሀገረ ስብከት ለሚኖረው የክርስቲያን ማኅበረሰብ መንፈሳዊና ማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጥ ፕሮግራም አቋቁማለች። ፕሮግራሙ የልህቀት ማዕከል ሲሆን በመርሃ ግብሩ፣ በሀገረ ስብከት ላሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ትምህርት እና ማህበራዊ ፕሮግራሞችን ከባህል ጋር የሚስማማ አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመ ነው።

መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እምነት፣ ትውፊት እና ባህል ለማስጠበቅ፣ ለማጠናከር እና ለማስተዋወቅ ይተጋል። በተጨማሪም መርሃ ግብሩ በሀገረ ስብከቱ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖችን አንድነት በማጠናከርና ማሰባሰብ ለማህበረሰቡ ድጋፍ እንዲያደርጉ ይጥራል። በተለይም ወጣቱ ትውልድ ክርስቲያናዊ እሴቶችን ተከትለው እንዲኖሩና አርአያ የሚሆኑበትን ድጋፍና ግብአት የሚያቀርብ የማህበረሰብ ማእከል ነው። የልህቀት ማዕከሉ የሚከተሉትን አገልግሎቶችን ይሰጣል።

ማህበራዊ አገልግሎት 1

ዓመታዊ የመስቀል እና የጥምቀት ማክበሪያ ማዕከል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሁለገብ አዳራሽ ዓመታዊው የመስቀልና የጥምቀት በዐል የሚከበርበት ማዕከል ይሆናል። በየጊዜዉ የሚገጥመንን የታላላቅ በዓላትን የማክበሪያ ቦታ ችግር በዚህ ማዕከል ይፈታል ብለን እናምናለን።

ማህበራዊ አገልግሎት 2

የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት

ቤተ ክርስቲያኒቱ በሀገረ ስብከት ውስጥ የምታደርገውን እንቅስቃሴ የመቆጣጠርና የማስተባበር ወሳኝ ሚና አለው። ጽ/ቤቱ ለቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ፣ ቀሳውስት እና ሌሎች የተለያዩ ግለሰቦች መንፈሳዊ መመሪያ መስጠት ፣ አስተዳደራዊ ድጋፍ እና ማህበራዊ ድጋፍ በመስጠት አገረ ስብከቱን ከማናቸዉም የዉጪ አካላት የሚያገናግኝ ይሆናል። በተጨማሪም የሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ፣ የዋሽንግተንን፣ የኦሪገንን እና የኢዳሆ አካባቢዎችን የሚያገለግል የሊቀ ጳጳሱ ኦፊሴላዊ ዋና መሥሪያ ቤት ሆኖ ያገለግላል። 

Hall

ማህበራዊ አገልግሎት 3

የነገረ-መለኮት ማሰልጠኛ ማዕከል

የነገረ መለኮት ትምህርት ቤት ዋና ዓላማ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ያሉ የነገረ መለኮት መምህራንን፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት እውቀትና ክህሎትን ማሳደግ ነው። በነገረ -መለኮት የአሰልጣኞች ሥልጠና – የሚሰጥ ሲሆን: አገልጋዮች በመረጡት ሙያ ሰልጥነው ቤተ ክርስቲያናቸውን በብቃት እንዲያገለግሉ የሚያስችል ይሆናል። ማሰልጠኛ ማዕከሉን በማሳደግ የነገረ መለኮት ኮሌጅ እንዲሆን ጥረት ይደረጋል ።

የነገረ መለኮት ማሰልጠኛ ማዕከል ቀስ በቀስ ወደ ሙሉ የነገረ መለኮት ኮሌጅ የሚያድግ ይሆናል።

ማህበራዊ አገልግሎት 4

የማኅበራዊ አገልግሎት ማእከል

ለልዩ ልዩ ማህበራዊ አገልግሎት ተስማሚ ሆኖ እስከ 2000 የሚደርሱ ግለሰቦችን የማስተናገድ አቅም ያለው አዳራሽ ይሆናል። ሁለገብ አዳራሹ ዘመናዊ መገልገያዎች ያሉት ሆኖ ፣ ለሠርግ ሥርዓት ፣ ለሥልጠና ፣ ለሴሚናሮች ፣ ለኮንፈረንስ ፣ ለምርቃት ፣ ለባህል ዝግጅቶች ፣ ኤግዚቢሽኖች ፣ ትምሕርቶች ፣ አገልግሎት የሚሰጥ ዘመናዊ የሕዝብ ማዕከልም ሆኖ ያገለግላል ።

Core Support Team

ዐብይ ድጋፍ ሰጪ ቡድን

ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ

(Information Technology)

ኢንጂነሪንግ እና ሪል እስቴት

(Engineering & Real Estate) 

የህግ አገልግሎት

(Legal)

Donate

Support Today

የዜል ቁጥር ይጠቀሙ (206)483-6078

ቼዝ ባንክ አካውንት ቁጥር Chase Bank A/C) 613265688

Connect

Join Community

Volunteer

Make an Impact

Support the EOTC Diocese in Washington, Idaho, and Oregon

ማዕከሉን ለመገንባት ሁላችንም እንረባረብ! አቅማችን የፈቀደውን ሁሉ እናድርግ ፦

ድጋፍ ለማድረግ በሚከተለው የሀገረ ስብከቱ የዜል ቁጥር ይጠቀሙ (206) 483-6078
ቼዝ ባንክ አካውንት ቁጥር Chase Bank A/C) —- 613265688

Help us fundraise for The important projects

Make a lasting impact on your community

እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም

2 ቆሮንቶስ 9:7